አቃቢ ሕግ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በሃያ ሁለት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትና ደጋፊዎች ላይ የመሠረተው ክስ በዝግ ችሎት እንዲካሄደ ያቀረበውን ጥያቄ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምደብ አራተኛ ወንጀል ችሎት በሙሉ ድምፅ ውድቅ አደርጎታል፡፡
አዲስ አበባ —
የፍርድ ሂደቱ በገለፅ ችሎት ቀጠሎ የአቃቢ ሕግ ምሰክሮቸ መሰማት ጀምሯል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ትናንት አቃቢ ሕግ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ አባላትንና ደጋፊዎችን ያጠቃለለው የሃያ ሁለት ተከሣሾች ክስ በዝግ ችሎቱ ላይ እንዲታይ ያቀረበውን ጥያቄና የተከሳሾች ጠበቆች ያቀረቡትን መቃወሚያ ክርክር እንደመረመረ ገልጿል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
በዝግ ችሎት እንዲታይ የተጠየቀው አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሃያ ሁለት የኦፌኮ አባላት ጉዳይ ውድቅ ተደረገ