አቃቤ ህግ፣ የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ አባላትን ከሰሰ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያምን ጨምሮ አስራ ሁለት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ አባላትን አቃቤ ህግ ሰላም በመንስት ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማሪያምን ጨምሮ አስራ ሁለት የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ዴሞክራሲ አባላትን አቃቤ ህግ ሰላም በመንስት ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል። አቃቤ ህግ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለመጀመሪያ ፍርድ ቤት ለቂርቆስ ምድብ ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ክስ መሰረት፣ ሚያዝያ ሃያ ቀን 2002 ዓም ከቀኑ በአምስት ሰዓት ላይ፣ በአንድ ነት ጽህፈት ቤት ዉስጥ፣ የፓርቲዉ አባላትና ሰራተኞች ስራ ላይ እያሉ፣ ድንጋይ በመወርወርና ሁከት በመፍጠር የወንጀል ተግባር ፍጽመዋል ብሎአል።
ፍርድ ቤቱ የአምስት ምስክሮችን ቃል ሰምቶ ጉዳዩን ለፌታችን ነሐሴ አስራ ዘጠኝ ቀጥሮአል።
ዝርዝሩን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያዳምጡ።