ብራዚል ውስጥ የሚካሄደው የዘንድሮው “ሪዮ ኦሎምፒክ 2016” ሊደረግ ሃምሳ ሰባት ቀናት ብቻ ቀርተውታል። እንደ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አገላለጽ ይህ ጊዜ ለአትሌቶች የመጀመሪያ ልምምድ ጊዜያቸውን አጠናቀው ለሁለተኛ ልምምድ የሚዘጋጁበት ነበር። በኢትዮጵያ ግን በአትሌቶችና በትሌቲክስ ፌደሬሽን መካከል በአትሌቶች ምርጫ በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ላይ ናቸው።
ለውዝግቡ መነሻ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ለምርጫ የሚያበቃውን መስፈርት ከአንድ ዓመት በፊት ማሳወቅ ሲገባው፤ አትሌቶቹ በቀደመው መስፈርት ዝግጅት ካደረጉና ለምርጫ ራሳቸውን ካዘጋጁ በኋላ ከምርጫው ውጤት እኩል አስታውቋል የሚል ነው። በተጨማሪም መስፈርቱም ከዚህ በፊት ያልነበረና ውጤት ለማምጣት ዋስትና የማይሰጥ ነው፣ እንዲሁም በአስር ቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ምርጫ መካሄዱን በመግልፅ በአጠቃላይ ምርጫውን ያካሄደው ኮሚቴ ብቃት የሌለውና በፌደሬሽን ውስጥ ያሉት አመራሮች የብቃት ማነስ ችግር አለባቸው የሚለው የበርካታ አትሌቶች ቅሬታ ነው።
ቅሬታ ካደረባቸው አትሌቶች መካከል አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት መሰለች መልካሙ ተጠቃሽ ናቸው። አትሌቶቹ 12 አባላት ያሉት አንጋፋ አትሌቶችን ስብስብ መርጦ ኮሚቴ አቋቁሟል። የዚህ ኮሚቴ
ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረስላሴ ነው።
ባልደረባችን ጽዮን ግርማ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴን፣አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና አትሌት መሰለች መልካሙን ፣የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ ስለሺ ብስራትና እንዲሁም ታደለ አሰፋና ሰኢድ ኪያር የተባሉ ጉዳዩን በስፋት ሲከታተሉ የቆዩ ሁለት የስፖርት ጋዜጠኞችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5