የሰሜን ወሎ ዞን ሦስት ከተሞች የዛሬ ውሎ

በሰሜን ወሎ ዞን እስካሁን ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል። በወልዲያ፣ በቆቦ በመርሳና የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን ትምሕርት ቤት መዘጋቱን ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሜን ወሎ ዞን ሦስት ከተሞች የዛሬ ውሎ

ከዐሥር ቀናት በፊት በወልዲያ ከተማ የጥምቀት በዓል በማክበር ላይ እያሉ የተገደሉ ሰዎችን በፀሎት ለማሰብ በዛሬው ዕለት በወልዲያ ከተማ የጧፍ ማብራት ሥነ ስርዓት እያከናወኑ ባለበት ወቅት ተኩስ እንደተከፈተባቸው ያነጋገርናቸው የወልዲያ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀውልናል።

በወልዲያ፣ በቆቦ በመርሳና የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ መቋረጡን ትምሕርት ቤት መዘጋቱንም ጨምረው ነዋሪዎቹ ጨምረው ተናግረዋል።

የአካባቢው ወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለፁልን ነዋሪዎቹ በአንፃሩ ደግሞ ወጣቶች እየታሰሩ መሆኑ ተናግረዋል

በእነዚህ ከተሞች በተከታታይ በነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞና ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉንና ንብረት መውደሙን ነዋሪዎችና መንግስት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ለዚህ አለመረጋጋት በመንግሥት በኩል ለሕዝቡ ጥያቄ በአፋጣኝ ምላሽ አለመሰጠቱ መሆኑን አስታውቋል። ሕይወታቸው ለጠፋውና አካላቸው ለጎደሉ ሰዎች የተሰማውን ሐዘን በመግለፅ መፅናናቱን ተመኝቷል። ግጭቶቹ መልካቸውን እንዲቀይሩ በተሰራው ሥራ ማንነታቸውን ብቻ ተስተውሎ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች ማዘኑንም የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

የዘገባውን ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።