የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከኦነግ አመራር አባላት ጋር "ግንኙነት አላቸው" ያላቸውን ሰባት ወጣቶች ከሰሰ

  • መለስካቸው አምሃ

ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ "እነ ኦሊያድ በቀለ" በሚል መዝገብ ከኦነግ አመራር አባላት ጋር ግንኙነት በማደረግ አባላትን በመመልመልና ሌሎችንም ድርጊቶች በመፈፀም የፀረ ዓዋጁን ድንጋጌዎች ጥሰዋል ሲል ሰባት ወጣቶችን ከሰሰ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ "እነ ኦሊያድ በቀለ" በሚል መዝገብ ከኦነግ አመራር አባላት ጋር ግንኙነት በማደረግ አባላትን በመመልመልና ሌሎችንም ድርጊቶች በመፈፀም የፀረ ዓዋጁን ድንጋጌዎች ጥሰዋል ሲል ሰባት ወጣቶችን ከሰሰ፡፡

ፍርድ ቤቱ የተከሳሾቹን የክስ መቃወሚያ ለመቀበል፣ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዛሬ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብአሥራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የክስ ማመልከቻ ሰባቱ ተከሳሾች የመደበኛውን የወንጀል ሕግና የፀረ ሽብር ዓዋጁን የተለያዩ ድንጋጌዎች እንደጣሱ ይናገራል፡፡

በተለይም በ2001 ዓ.ም. የወጣውን የፀረ ሽብር ሕግ በመተላለፍ በዋና ወንጀል አድራጊነትና ወንጀሉ የሚያመጣውን ውጤት በጋራ እንደተቀበሉም ይጠቁማል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከኦነግ አመራር አባላት ጋር "ግንኙነት አላቸው" ያላቸውን ሰባት ወጣቶች ከሰሰ