ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በሰመራ ከተማ

  • ቆንጂት ታየ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል። ከህዝቡ ጋርም ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ጉብኝት አድርገዋል። ከህዝቡ ጋርም ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ እንዲገኙ የክልሉ አስተዳደር የጋበዛቸው ሰዎች ጥያቄዎቻችን በሚገባ ሊያቀርቡልን የሚችሉ ስላልሆኑ ራሳችን ማቅረብ እንፈልጋለን ባሉ ወጣቶችና ፖሊሶች ጋር ግጭት ከአዳራሹ ውጭ ተፈጥሮ እደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪ ገልጸውልናል። ብዙዎች ተደብድበዋል ታስረዋል ብለዋል።

አንድ የክልሉ አስተዳደር ባለስልጣን ግን ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሸኝተናል። ደጁ ላይ ተከሰተ የተባለውን አላየሁም አላውቅም ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በሰመራ ከተማ