የኢህአዴግ እና የተቃዋሚዎች ንግግር

ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

“የፖለቲካና የሕሊና አስረኞች የሉም” - የኢህአዴግ ዋነኛ ተደራዳሪ ሽፈራው ሽጉጤ፡፡

ገዥው ኢህአዴግና አሥራ ስድሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአጀንዳ ነጥቦች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ቀጥለዋል፡፡

ኢህአዴግ ፀረ-ሽብር ሕጉን ጨምሮ በተለያዩ አዋጆች ላይ ለመነጋገር ተስማምቷል፡፡ በፖለቲካ እና በሕሊና እስረኞች ጉዳይ ላይ ግን እንደማይደራደር ግልፅ አድርጓል፡፡

“የፖለቲካና የሕሊና አስረኞች የሉም” ብለዋል የኢህአዴግ ዋነኛ ተደራዳሪ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፡፡

ተቃዋሚዎች ግን “የፖለቲካና የሕሊና እስረኞች አሉ” ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ኢህአዴግ ከ16 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር በፀረ ሽብር ሕጉና በሌሎች አዋጆች ላይ ለመነጋገር ተስማማ