በሽብር ወንጀል ተከስሰው በክርክር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ተከሣሾች ለፍርድ ቤት ሲሰጡ የቆዩትን ቃል ዛሬ አጠቃልለዋል።
አዲስ አበባ - ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
በሽብር ወንጀል ተከስሰው በክርክር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና ሌሎችም ተከሣሾች ለፍርድ ቤት ሲሰጡ የቆዩትን ቃል ዛሬ አጠቃልለዋል።
የመከላከያ ምሥክሮችን ለመስማት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ሰላማዊ ትግል የሚመራ ”የድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ” ዛሬ በአዲስ አበባው የአንዋር መስጅድና በሌሎችም ከተሞች የመፍትሔ አፈላላጊውን ኮሚቴ የፍርድ ሂደት በማስመልከት ”ፍትህ ተነፍገን ትግላችን አይቆምም” የሚል መፈክር በማንገብ ሰላማዊ ተቃውሞ ማካሄዱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሣምንቱ በየመስጅዶች ይካሄድ የነበረው ተቃውሞ ረዘም ላለ ጊዜ ቆሞ እንደነበር ይታወቃል።
ካለፉ ሁለት ሣምንታት የጁምዓ ሶላት ወዲህ ግን መቀጠሉን “የድምፃችን ይሰማ” ንቅናቄ ተወካዮች ገልፀዋል ባልደረባችን አዲሱ አበባ በመስጅዱ ሰላማዊ ተቃውሞ ከተካፈሉ አንዱን አቶ መሃመድ አብደላን በስልክ አነጋግሯል።
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳጥጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5