አዲስ አበባ ላይ ለማካሄድ ታስቦ የነበረው የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የሰደቃ ወይም የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ መካሄዱን አንድ ሁኔታውን በቅርብ የተከታተለ እማኝ ተናግሯል፡፡
(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)
ሰደቃው የተካሄደው በታላቁ አንዋር መስጊድ ቁጥሩ እጅግ የበዛ ምዕመን በተገኘበት ሲሆን ቀደም ሲል በዋናነት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረበት አወሊያ መስጊድ አካባቢ በፀጥታ ኃይሎች የተከበበ በመሆኑ ፕሮግራሙ ወደ አንዋር መስጊድ እንዲዛወር ሰዉ በመስማማቱ መሆኑን እማኙ አክሎ ጠቁሟል፡፡
በዛሬውና በሌሎችም መስጊዶችና አካባቢዎች በተካሄዱ ተመሣሣይ የሙስሊም አማኒያን የፀሎትና የስብሰባ ሥነ-ሥርዓቶች ላይ ክርስቲያኖችም በእንግድነት እየተገኙ ሥነ-ሥርዓቶቹን መከታተላቸውንም ገልጿል፡፡
ስለዛሬው ፕሮግራምና ስላለውም አጠቃላይ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ደውለን ነበር፡፡ የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትንም ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አድርገናል፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )