(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)
የኢትዮጵያ ህዝብ የከፍተኛውን የ“መራኂ መንግሥት” ባለሥልጣን አቶ መለስ ዜናዊ ትክክለኛ የጤና ሁኔታ እስካሁን በግልፅ የሚያውቀው የለም።
በኒው ኦርሌአንስ ሉዊዝያና ቱሌን ዩኒቨርሲቲ የህዝባዊና ህገመንግሥታዊ ህግ ፕሮፌሰር አድኖ አዲስ በሰጡን ግምገማ “ሕዝብ ስለ መሪዎች ጤና ለማወቅ ያለው መብት ምን ያህል ነው?” የሚለው ጥያቄ ቀላል አይደለም ብለዋል። ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰፈነባቸው አገሮች መሪዎች ሥልጣን ከመያዛቸውና ከያዙም በኋላ ህዝቡ ስለጤናቸው ሁኔታ የማወቅ መብት አለው ብለዋል።
ፕሮፌሰር አድኖ እንዲህ ዓይነቶቹ የሕዝብ መብቶች እንዲከበሩ ግን የዴሞክራሲ ምሶሦ የሚባሉ ሦስት ነጥቦች መሟላት አለባቸው ብለዋል። ሲዘረዝሯቸውም፤ አንደኛ፣ ከመንግሥት ቁጥጥር ፍፁም ነፃ የሆነ መገናኛ ብዙኃን፤ ሁለተኛ፣ የተደራጀና ነፃ የሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚ፣ ሦስተኛ፤ ገለልተኛና ነፃ ፍርድ ቤትና ዳኞች መቋቋም አለባቸዉ ብለዋል፡፡
“የሦስቱ ነፃነቶች ዋና ዓላማ መንግሥት በሕግ እንዲያስተዳድር፣ ሰብዓዊ መብቶችን እንዳይጥስ፣ የሚያፀድቃቸው ፖሊሲዎች በይፋ ወጥተው እንዲገመገሙ፣ በአጠቃላይ መሪዎቹ ለህዝቡ ማለትም ለቀጣሪያቸው ተጠያቂ እንዲሆኑ ያስገድዳል” ብለዋል።
ለተጨማሪ ዝርዝር ፕሮፌሰር አድኖ ለትዝታ በላቸው የሰጡትን ግምገማ ያድምጡ።
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )