ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የማህፀንና የፅንስ ከፍተኛ ሃኪሞች ኣንዱ የሆኑት ዶ/ር አማኑኤል ገሰሰው የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን የላቀ የሽልማት ደረጃ ኣግኝቷል።
መቀለ —
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት የማህፀንና የፅንስ ከፍተኛ ሃኪሞች አንዱ የሆኑት ዶ/ር አማኑኤል ገሰሰው የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን የላቀ የሽልማት ደረጃ ኣግኝቷል።
በዚሁም መሰረት በጤናው ዘርፍ ልዩ የሕይወት ዘመን ሽልማት እና የሞያ ስነ ምግባር ኣምባሳደር ተሰጥቷቸዋል።
ሃኪሙ ባለፉት 26 ዓመታት ህክምና በመስጠት የብዙዎች እናቶች እና ሕፃናት ሕይወት በማዳን በኩል ኣመርቂ ውጤት ኣስገኝቷል። በሁለተኛ ደረጃም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማስተማር በርካታ የጤና ሊቃውንት ያፈሩ ታላቅ ምሁር ናቸው።
ዶክተር ኣማኑኤል በምርምር በኩልም ተሰማርተው በመስራት ያገኙትን ውጤት በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገሮች የተለያዩ የጤና መጽሔቶች ታትሞ ለንባብ ቀርቧል።
ከስራ ልምዳቸው በመነሳትም “ወለላ” የተሰኘ በተለይም በእናቶችና ሕፃናት የጤና ኣጠባበቅ ዙርያ የሚያስተምር በኣማርኛ እና በትግርኛ መጽሐፍ ኣሳትመውም ለንባብ ኣብቅቷል።
ዶክተር ኣማኑኤል በመቐለ “ቃል ኪዳን የግል ሆስፒታል” ባለቤት ሲሆኑ በርካታ ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ኣስተባብረው በማሰራት ላይ ይገኛሉ።
በግርማይ ገብሩ ከመቀለ የላከውን ዘገባ ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5