የኢትዮጵያን ብዙኀን መገናኛ ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ዐዋጅ ከፍተኛ ትችት ቀረበበት

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያን ብዙኀን መገናኛ ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ዐዋጅ ከፍተኛ ትችት ቀረበበት

በርካታ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣ የሲቪክ ተቋማትና የጋዜጠኞች ሞያ ማኅበራት የመገናኛ ብዙኅን ዐዋጅ ማሻሻያ ረቂቁን ተቃወሙ።

የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባዘጋጀው ውይይት ላይ የተገኙ በአብዛኛው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ተወካዮች፣ ረቂቁ በነባሩ ዐዋጅ የተደነገጉ የመገናኛ ብዙኅን ነጻነቶችን ወደ ኋላ የሚመልስ መኾኑን ጠቅሰው፣ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኅን ባለሥልጣን በበኩሉ፣ “ማሻሻያው ነጻነትን የሚገድብ ሳይኾን የሕግ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ያለመ ነው" ሲል ትችቱን ተከላክሏል።