በኢትዮጵያ በወባ በሽታ የተነሣ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ27 በመቶ እንደጨመረ ያስታወቁት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ3ነጥብ3 ሚሊዮን በላይ ሕሙማን መኖራቸውን ገልጸዋል።
ከሕሙማኑ የሚበዙት በኦሮሚያ ክልል እንደሚገኙ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበርያ ቢሮ /UN-OCHA/ ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት ሲጠቁም፣ በዐማራ እና በሲዳማ ክልሎችም የወባ በሽታ ስርጭት እንደጨመረ አመልክቷል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡