በስዋሂሊ "Watu Wate" በአማርኛ "ሁላችንም” የተሰኘው አጭር ፊልም ለኦስካር ታጨ

Your browser doesn’t support HTML5

ፊልሙ የተሰራው በጀርመናዊቷ የፊልም ተማሪ ሲሆን፤ እ.አ.አ. በ 2015 ዓ.ም ከናይሮቢ ማንዴራ ወደተባለች የኬንያ አንዲት ግዛት ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የደረሰበትን የአሸባሪዎች ጥቃት ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ ነው። ይህ ፊልም ለዘንድሮው የሆሊውዱ የኦስካር ሽልማት እጩ ከሆኑት ፊልሞች ውስጥ አንዱ ነው።