ጋዜጠኞቹና ብሎገሮቹ በቀጠሮው መሠረት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ

  • መለስካቸው አምሃ

ጋዜጠኛተስፋዓለም ወልደየስ እና ሌሎች የዞን 9 ፀሐፊዎች ወደ ችሎት ሲወሰዱ /ፎቶ ፋይል - ከአዲስ ስታንዳርድ የተገኘ/

ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች መካከል ስድስቱ ትናንት ቅዳሜ፤ ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/

Your browser doesn’t support HTML5

ጋዜጠኞቹና ብሎገሮቹ በቀጠሮው መሠረት ችሎት ሳይቀርቡ ቀሩ

ፖሊስ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ ከያዛቸው ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት አምደኞች መካከል ስድስቱ ትናንት ቅዳሜ፤ ሐምሌ 5/2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡

የትናንቱ ቀጠሮ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ፖሊስ በጠየቀው መሠረት ፈርድ ቤቱ የመጨረሻ ሲል የፈቀደው ቀጠሮ ሲሆን የተያዙት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ያቀረቡበትን ምክንያት ፍርድ ቤቱም፣ ፖሊስም አቃቤ ሕግም አለመግለፃቸውን ጠበቃቸውን አቶ አምሃ መኮንንን ጠቅሶ መለስካቸው አምሃ ዘግቧል፡፡

የቀሩት ሦስቱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ነገ ሰኞ፤ ሐምሌ 7/2006 ዓ.ም ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡