በጋዜጠኞቹና በብሎገሮቹ ላይ ክሥ ተመሠረተ

  • መለስካቸው አምሃ

ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ለሦስት ወራት ያህል ክስ ሳይመሠረትባቸው ታስረው በቆዩት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሃፊዎች፤ እንዲሁም በአንድ ሌላ ተጠርጣሪ ላይ አቃቢ-ህግ ዛሬ የአሸባሪነት ክሥ ከፈተ።

የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/

Your browser doesn’t support HTML5

በጋዜጠኞቹና በብሎገሮቹ ላይ ክሥ ተመሠረተ

ለሦስት ወራት ያህል ክስ ሳይመሠረትባቸው ታስረው በቆዩት ዘጠኝ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሃፊዎች፤ እንዲሁም በአንድ ሌላ ተጠርጣሪ ላይ አቃቢ-ህግ ዛሬ የአሸባሪነት ክሥ ከፈተ።

ክሡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክሡ የተመሠረተባቸው በፈቃዱ ኃይሉ፤ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማኅሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ሲሆኑ በአንደኛ ተከሣሽነት የተጠቀሰችው ሶልያና ሺመልስ የተከሰሰችው በሌለችበት ነው፡፡

ክሦቹ በንባብ ከተሰሙ በኋላ የተመሠረተው ክሥ በሽብር አዋጅ የቀረበ ስላልሆነ ተጠርጣሪዎቹ የዋስ መብታቸውን ሊነፈጉ አይገባም ሲሉ የተከሳሽ ጠበቆች ተከራክረዋል።

አቃቢ-ህግ ተቃውሟል፤ ፍርድ ቤት ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጥሮ ሰጥቷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ችሎቱ ላይ ተገኝቶ የነበረውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡