የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ

  • እስክንድር ፍሬው
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የፅህፈት ቤታቸውን ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጡ።

የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር በዋቢነት የጠቀሰው 'The Times Of Israel' /ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል/ “የኢትዮጵያው መሪ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው በመመለሱ ሂደት ዕገዛ ለማድረግ ተስማምተዋል” ሲል ነው ሰሞኑን የዘገበው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፅህፈት ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን የስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ጉዳይ እንዲያውም በሁለቱ መሪዎች ውይይት አልተነሳም ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ