የጸጥታ ስጋት ያሳሰባቸው አንዳንድ የአመት በዓል ተጓዦች ከቤተሰብ ጋር አያከብሩም

ፎቶ ፋይል፦ታዳጊዎቹ አዲስ ዓመትን ለማክበር አበቦች ከመስክ እየሰበሰቡ፣ ላሊበላ፣ የኢትዮጵያን

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የቀጠለው የጸጥታ ችግር ስጋት፣ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጓዝ እና የአዲስ ዓመት በዓልን ባሰቡት መንገድ ለማክበር እንዳላስቻላቸው አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በተለይም በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ምክንያት፣ መንገድ ላይ በሚፈጠር የተኩስ ልውውጥ ጉዳት ሊደርስብን ይችላል ያሉ አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች፣ በዓሉን በነጻነት ተንቀሳቅሶ ለማሳለፍ እንደተቸገሩ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን በበኩሉ ባለፉት ሁለት እና ሶስት ቀናት ውስጥ ኦሮሚያና አማራ ክልልን ጨምሮ፣ ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለበዓል የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን አመልክቶ የተጓዦችን ጥያቄ ለማሟላትም ተጨማሪ ተሸከርካሪዎችን ወደ ስምሪት ማስገባቱን ጠቅሷል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የጸጥታ ስጋት ያሳሰባቸው አንዳንድ የአመት በዓል ተጓዦች ከቤተሰብ ጋር አያከብሩም