በኢትዮጵያ የከበደ የረሃብ አደጋ ሥጋት ተደቅኗል

ኢትዮጵያ ውስጥ የአደጋ ጊዜ “ምግብ ክምችት እየተሟጠጠ ነው” ሲሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እያስታወቁ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የአደጋ ጊዜ “ምግብ ክምችት እየተሟጠጠ ነው” ሲሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እያስታወቁ ነው፡፡

ሃገሪቱ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ በከበደ ድርቅ ምክንያት ለረሃብ ለተጋለጠ ወደ ስምንት ሚሊየን ለሚጠጋ ሰው የምታቀርበው ምግብ በጎተራዋ እንደማይኖር ተነግሯል፡፡

ቁጥሩ በይፋ ባይነገርም አሁን “አለ” በሚባለው ወደ ስምንት ሚሊየን የሚጠጋ ቁጥር ያለው ረሃብ ያፈጠጠበት ሰው ላይ ሌሎች ሁለት ሚሊየን በመጭው ወር ውስጥ እንደሚታከሉ የመንግሥቱንና የሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮቹን ጥናት፣ እንዲሁም አኀዛዊ ቀመሮች ያጣቀሰው የሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገባ ጠቁሟል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የከበደ የረሃብ አደጋ ሥጋት ተደቅኗል

"በሕይወቴ እንዲህ ያለ ነገር አይቼ አላውቅም፤ እርዳታ ካላገኘን እኛም እንዳለቁት እንሥሶቻችን እናልቃለን" ብላለች ተፈናቃይዋና በዋርደር መጠለያ የፈረንሣይ ዜና ወኪል ያነጋገራት የሰላሣ ዓመቷ ቃራት ባርት፡፡

እስከ ፊታችን ሐምሌ የዘጠኝ መቶ ሰላሣ ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት ኢትዮጵያ ብታሳስብም እስከ አሁን ያገኘችው ከጠየቀችው ግማሽ ያህሉን ብቻ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ሰሞኑን ወደ ሶማሌ ክልል ሄደው የዋርዴርን አካባቢ የጎበኙት በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ መርኃግብር (WFP) ተጠሪ ጆን አይሊየፍ "ያለንበት ሁኔታ እጅግ አስፈሪ ነው" ብለዋል ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፡፡

"የኢትዮጵያ መንግሥት ክፍተቱን ለመሙላት የተቻለውን ሁሉ እያደረገ" ነው ያሉት የሕፃናት አድን ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ዳይሬክተር ጆን ግራሃም ድኃ መንግሥት መሆኑንም አስታውሰው "ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በጥረቱ ውስጥ የመግባት ኃላፊነት አለበት" ሲሉ ከኤኤፍፒ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጥሪ አሰምተዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የከበደ የረሃብ አደጋ ሥጋት ተደቅኗል