በኢትዮጵያ የ274 ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት ፀደቀ

  • እስክንድር ፍሬው

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብዱአልዚዝ አህመድ

ለ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት 274 ቢሊዮን ብር መፅደቁን የኢትዮጵያ የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለ2009ዓ.ም የተመደበው የ274 ቢሊዮን ብር የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንጂ ያነሰ አለመሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ድርቁ በበጀቱ ላይ ተፅዕኖ አለማሣደሩን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ሃጂ ኢብሳ ገልፀዋል፡፡

የ2009 ዓ.ምን በጀት ረቂት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ያቀረቡትት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብዱአልዚዝ አህመድ ናቸው።

ከተጠየቀው የ274 ቢሊዮን ብር በጀት ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ድህነት ተኮር በሆኑ ዘርፎች ላይ እንደሚውልም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

በጀቱን በተመለከተ ለአሜሪካ ድምፅ ተጨማሪ ማብራርያ ከሰጡት የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ከአቶ ሃጂ ኢብሳ ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የ274 ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት ፀደቀ