20 አመታት የፌደራላዊ አገዛዝ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አገዛዘ 20ኛ አመት በአሉን ባከበረበት በአሁኑ ወቅት ባለፉት ሀያ አመታት ውስጥ ተከናወኑ ወይም አልተከናወኑም ስለሚባሉት የአስተዳደር፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ሌሎችም ጉዳዮች እንዲያብራሩል አቶ ሶፋንያ አለሙንና ዶክተር መረራ ጉዲናን ጋብዘናል። አቶ ሶፋንያ በፌደራል የፍትህ አካላት ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጣኝና የቅድመ ስራ ስልጠና አስተባባሪ ናቸው። ዶክተር መረራ ጉዲና ደግሞ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ዲሞክራስያዊ መድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ድርጅት መሪ ናቸው።

"የዜጎች ዲሞክራስያዊና ሰብኣዊ መብቶች ህገ-መንግስታዊ ዋስትና አግኝተው በቛንቛቸው የመናገርና የመዳኘት መብታቸው እንዲከበርላቸው ሆኗል። የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር በታሪካቸው የመኩራት መብታቸው በህግ አግባብ እንዲረጋገጥላቸው ሆኗል" በማለት ስለ ኢሀአዴግ ስኬት ገልጸዋል።

ዶክተር መረራ በበክሉላቸው "ፌደራሊዝም መጣ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ መሰረታዊ የፌደራላዊምም ሆነ የዲሞክራሲ ጥያቄዎችን መመለስ ያልቻለ የፖለቲካ ስርአት ነው ያለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ አልባ ፊርደራሊዝም ነው ያለው። ፓርቲንና መንግስትን አንድ የሚያደርግ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ነው" በማለት አቶ ሶፋንያ ያሉትን ተጻረዋል።