“ዋናው የሚያሳስበን ነገር ጸሃፊዎችን ለማፈን ብሔራዊ ጸጥታ ወይም ደህንነት የሚባለው ሰበብ እንደ መሳሪያ ሥራ ላይ እየዋለ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን፤ በሌሎች የአፍሪቃ አገሮችና በዓለም ዙሪያም እየተስፋፋ መምጣቱ ነው።”
ዋሽንግተን ዲሲ —
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የዘንድሮው የPEN CANADA የሰብዓዊ መብት ሽልማት ባለቤት ሆነ።
ለደራሲያንና ጋዜጠኞች መብት የቆመው ይህ ዓለም አቀፍ የጸሃፊዎች ቡድን ይፋ እንዳደረገው እስክንድር በዛሬው ምሽት በቶሮንቶ ካናዳ በሚካሄደው ሰላሳ ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የደራሲያን ክብረ በዓል መክፈቻ ላይ በሌለበት የዓመቱን የክብር ሽልማት ይጎናጸፋል።
ከቡድኑ የኮምዩኒኬሽን አስተባባሪ ብራንደን ደ ኬሪስ (Brandon de Carries) እና ከእስክንድር ባለቤት ከሰርካለም ፋሲል ጋር ሽልማቱን መነሻ በማድረግ የተካሄደ ቃለ ምልልስ ተንተርሶ የተቀናበሩትን ዘገባዎች በተከታታይ ቀጥሎ ያገኛሉ።
ከብራንደን ደ ኬሪስ (Brandon de Carries)ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ ተንተርሶ የተጠናቀረ ዘገባ ከዚህ ከተያያዘው የድምፅ ፋልይ በመጫን ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በተጨማሪም አሉላ ከበደ ከሰርካለም ፋሲል ጋር ቃለ ምልልስ በማካሄድ ያጠናቀረውን ዘገባ ከዚህ በታች ያለውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5