የኤርትራ አብራሪዎች አይሮፕላን ይዘው ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሲራጅ ፈጌሳ ተናገሩ

ኢትዮጵያና ኤርትራ

የኤርትራ አየር ኃይል ንብረት የሆነች አይሮፕላን ሁለት ፓይለቶችን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባቷን እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ማሳረፏን የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ትላንት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ከኤርትራ ከአርባ እስከ ሃምሣ የሚጠጉ ወታደሮች በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ፤ በዛው ልክ ሲቪሎችም ይገባሉ፤ ምናልባት የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በሰማይ መምጣቱ ብቻ ነው" ብለዋል፡፡

የኤርትራን መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ይሁንና የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለእንግሊዝ የዜና አውታር - ቢቢሲ በሰጡት መግለጫ ዜናውን "ውዳቂ" ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኤርትራ አብራሪዎች አይሮፕላን ይዘው ኢትዮጵያ መግባታቸውን ሲራጅ ፈጌሳ ተናገሩ