ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ለመኖሪያ ከተሰጣቸው ህንፃ በታጠቁ የጣልያን ወታደሮች እንዲለቁ ተደረጉ
Your browser doesn’t support HTML5
በጣልያን ሮም ከተማ በጥገኝነት ይኖሩ የነበሩ ከ800 በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ለአራት አመታት ከኖሩበት በጣልያን ፖሊሶች ተገደው እንዲወጡ ተደረገ። ቅዳሜ አጥቢያ ላይ ነው በእንቅልፍ ላይ ሳሉ ነው በታጠቁ ፖሊሶች እየተዋከብቡ ጊዜያዊ መኖሪያቸውን እንዲለቁ የተገደዱት። ስደተኞቹ በሮማ ከተማ መንገድ ላይ መዋል ማደር ከጀመሩ ቀናቶች መቆጠራቸውንና መፍትሄው በመዘግየቱ ምክንያት ቅር መሰኘታቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።