በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ውጊያ እንደነበር የሁለቱም ሀገሮች መንግስታት አስታወቁ

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
    ግርማይ ገብሩ

የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኔ 5 ቀን ጥቃት ሰንዝሯል ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የኤርትራ መንግስት ለማጥቃት ያደረገውን ሙከራ ቀልብሰናል ብለዋል።

በተያያዘ ዜና፥ በሰሜን ኢትዮጵያ፥ በትግራይ ምሥራቃዊ ክልል በተለይ በገርሁ ስርናይ እና ዛላአምበሳ የገጠር አካባቢዎች ነዋሪዎች ትላንት ከንጋቱ 10 ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ መስማታቸውን በድምበር ከተሞች የሚኖሩ የዐይን ምስክሮች ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዩ ገለፁ።

ግርማይ ገብሩ በስልክ ያነጋገራቸው በድምበሩ አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች እንደሚገልፁት ሕብረተሰቡ በተለይም ዛሬ ተረጋግቶ ዕለታዊ ኑሮውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ውጊያ እንደነበር የሁለቱም ሀገሮች መንግስታት አስታወቁ