የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።
ዋሺንግተን፤ ዲሲ —
የትረምፕ አስተዳደር የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ጋብዟል።
የጥሪው አጀንዳ የኅዳሴ ግድብ አሞላልና በዓባይ ውኃ አጠቃቀም ላይ በካይሮና በአዲስ አበባ መካከል አለ የሚባለው አለመግባባት መሆኑ ተገልጿል።
ስብሰባውን እንዲጠሩ ለፕሬዚዳንት ትረምፕ ጥሪ ያቀረቡት የግብፁ አብዱልፋታህ ኤል ሲሲ ናቸው።
ጉዳዩ በቴክኒክ ባለሙያዎች የተያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያና ሱዳን የሦስተኛ ወገን አደራዳሪ በማስገባት ሃሳብ እንደማይስማሙ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የተናገሩት የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጋበዙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን መሆኑንና የድርድርም አለመሆኑን ተናግረዋል።
ለሙሉው ቃለ ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5