ጠብ ሲልና ዳመና ሲርቅ: የኢትዮጵያ ግብርና ፈተናዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በዝናብ እጥረት የተነሳ በተከሰተው ድርቅ 8.2 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ ዋስትና ችግር እንደገጠማቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምጣኔ ሀብት አማካሪ አቶ ንዋይ ገብረዓብ ገልጸዋል። መንግስታቸው የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል በሚጥርበት ወቅት የተከሰተው ድርቅ የገበሬዎችን ኑሮ ማወኩንና መፈታተኑን የገለጹት የምጣኔ ሀብት አማካሪ፤ በምርት ላይ የደረሰው ጉዳት በውል የሚታወቀው ሰብል ሲሰበሰብ ነው ብለዋል።