ዋሺንግተን ዲሲ- አዲስ አበባ —
Your browser doesn’t support HTML5
ኢቦላን ለመዋጋት ወደ ምዕራብ አፍሪካ ይጓዛሉ ለተባሉት ከ200 በላይ ሐኪሞችና ሌሎችም ባለሙያዎች አሁን በአዲስ አበባ ሂልተን አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡
የኢትዮጵያን የኢቦላ ምላሽ የሚያስተባብረ ው የማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አቤል የሻነህ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ሽኝቱ የተዘጋጀው ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዘማቾች ነው፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ ባለሙያዎች ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚጓዙት የአፍሪካ ኅብረት ፀረ-ኢቦላ ምላሽ አካል ሆነው እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ እስከአሁን የኢቦላ ተጠርጣሪም ሆነ የወረርሽኙ ምልክት ኢትዮጵያ ውስጥ አለመታየቱ በአይሮፕላን ጣቢያዎች ላይ እየተካሄደ ያለው ፍተሻና ክትትልም እንደቀጠለ መሆኑን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡