Your browser doesn’t support HTML5
“ህንፃዎቹ የተወሰነ የርዕደ መሬት መጠንን ይቋቋማሉ” መንግሥት
በኢትዮጵያ ያሉት አብዛኞቹ ህንፃዎች በዲዛይን ወቅት በሚፈጠር ክፍተትና በግንባታ ጥራት ጉድለት የተነሳ ለርዕደ መሬት አደጋ የተጋላጡ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ህንፃዎች ርዕደ መሬትን እንዲቋቋሙ በሚያስችል መልኩ ዲዛይን እንዲደረጉ አስገዳጅ የህንፃ ኮድ ብታዘጋጅም፣ መስፈርቱን ከመከተል አኳያ ክፍተቶች አሉ ብለዋል፡፡ መንግሥት በበኩሉ፣ “በህንፃዎች ግንባታ ወቅት፣ መስፈርቱ እንዲተገበር ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው፣ ህንፃዎቹም የተወሰነ የርዕደ መሬት መጠንን የመቋቋም አቅም አላቸው” ይላል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።