በአፋር ክልል፣ ዞን ሦስት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል 5.1 የተመዘገበ ርእደ መሬት መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊሲክስ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታወቀ።
Your browser doesn’t support HTML5
የተቋሙ ተመራማሪ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ፣ ርእደ መሬቱ ያስከተለው ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
ርእደ መሬቱ ለንብረት ውድመት ምክንያት ኾኗል ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ችግሩ አሳሳቢ ስለኾነባቸው ወደ ሌላ አካባቢ መሸሻቸውን ተናግረዋል።
የአዋሽ ፈንታሌ ግብርናና አደጋ መከላከል ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ሰዎችን ወደሌሎች አካባቢዎች የማንቀሳቀስ ሥራ መጀመሩን አረጋግጧል።