ደቡብ ኦሮሚያ የድርቁ ጫና አሁንም እየከፋ ነዉ

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ ኦሮሚያ የድርቁ ጫና አሁንም እየከፋ ነዉ

በኦሮሚያ ክልል ደቡባዊ ክፍል ድርቁ ያስከተለው ጫና የከፋ መሆኑን የጉጂ ዞን አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ልቤን ደበሶ በዞኑ በድርቅና በፀጥታ ችግር ምክኒያት ለችግር የተጋለጡ ከአምስት መቶ ሰባ ሺህ በላይ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት የእርዳታ ማስተባበርያ ቢሮም፣ በድርቅ የተጠቁ የኢትዮጵያ ክልሎች በኮሌራ ወረርሺኝም እየተጎዱ መሆኑን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ለአምስት ተከታታይ ወቅቶች ዝናብ ባለመኖሩ ምክኒያት የተባባሳው የቦረና ድርቅ እስካሁን 3.3 ሚልየን እንስሳት መጨረሱን የዞኑ አስተዳደር ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል።

ቦረና ውስጥ ድርቅ መበርታቱንና ነዋሪዎቹ በምግብ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ጠቅሰን በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

በተጨማሪም ወደ ስምንት መቶ ሺህ የሚሆን ሰው የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውና ከእነዚህም ውስጥ አዛውንቶችና ሕፃናት በረሃብ እየተጎዱ መሆናቸውና የሚደርሰው የእርዳታ እህልም እጅግ አነስተኛ መሆኑን የቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ነዋሪዎችና በአካባቢው የሚሰሩ የጤና ባለሞያ ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸው አይዘነጋም።

የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።