ነዋሪዎቹ ስለድርቁ እና ረሃቡ ይናገራሉ

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከገጠሟት ሁሉ በከፋ ሁኔታ በድርቅ እንደተመታች እየተነገረ ነው። በተለይ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ እንዲሁም በአማራ ክልል ከፍተኛ ርብርብ ካልተደረገ ሁኔታው ተባብሶ ወደ ከፍተኛ ረሃብ ሊቀየር ይችላል የሚል ስጋት አለ። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ የአፋር፣የሁምራ እና የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ነዋሪዎችን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናክሯል፡፡

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከገጠሟት ሁሉ በከፋ ሁኔታ በድርቅ እንደተመታች እየተነገረ ነው። ይኽ ድርቅ የእርሻና የግጦሽ መሬቶችን ማራቆቱን፣ ከብቶች መሞታቸው በዚህም ምክንያት በሰው ልጆች ላይ ረሃብ መከሰቱ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ ጠቋሚ የኾኑ መረጃዎች ቢወጡም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል፤ “ድርቁ ኤልኒኖ ባስከተለው የዝናብ እጥረት ምክንያት የመጣ ነው፣ በጥቂት መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ርዳታ ይፈልጋሉ እንጂ ረሃብ የለም፡፡’’ የሚል መግለጫ ሲሰጥ ቆይቶ ነበር። አኹን በይፋ መገለፅ ከጀመረ በኋላ በኢትዮጵያ 8.2 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ለጋሽ ድርጅቶች ርዳታ እንዲሰጡ ጠይቋል። አሁን በይፋ ርዳታ እየተሰጠ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በተስፋ በአፋር ፣ በአማራ ፣በሶማሌ ፡ በትግራይ በደቡብ በምስራቅና በምዕራብ በሓረርጌ ያሉ ሰዎች የረሃቡ ሰለባዎች ኾነዋል። ድርቁ በከፋ ሁኔታ ስላጠቃቸውም አስቸኳይ የምግብና የሕክምና ርዳታ ይፈልጋሉ።

ድርቁ በአስከፊ ሁኔታ ከተባባሰባቸው አካባቢዎች አንዱ አፋር ክልል ነው፡፡

በዚህ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎችን አነጋግራ ጽዮን ግርማ የሚከተልውን ዘገባ ሠርታልች፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የአፋር ክልል ነዋሪዎቹ ስለድርቁ እና ረሃቡ ይናገራሉ

ሁመራ አካባቢ ስላለው ድርቅ ደግሞ አዲሱ አበበ በግብርና ሞያ የሚተዳደሩትን አቶ ገሞራ ገሠሠውን አነጋግሯል።በሁመራ ዞን አደባይ፣ ራውያን፣ ሴንትራል፣ በረከት በሚባሉት ስፍራዎች ድርቁ የከፋ እንደኾነ አቶ ገሞራ ይናገራሉ። ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ሁመራ ነዋሪ ስለድርቁ እና ረሃቡ ይናገራሉ

በሞዕራብ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ዝናቡ ወቅቱን ጠብቆ ባለመጣሉ ድርቅና የምግብ እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡የኦሮመኛ ክፍል ባልደረባችን ጃለኔ ገመዳ ያነጋገረቻቸው አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጭሮ ወረዳ ነዋሪ፤’’በረሃብ ምክንያት የሞት ሰው አለ” ብለዋታል፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የሞዕራብ ሐረርጌ ነዋሪዎች ስለድርቁ እና ረሃቡ ይናገራሉ