ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች በሁለት ቢሊየን ብር ሆስፒታል ሊገነቡ ነው

  • እስክንድር ፍሬው

ጤና

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች በሁለት ቢሊየን ብር ሆስፒታል ሊገነቡ ነው

ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል በመቶ ሚሊየን ዶላር ወይም ወደ ሁለት ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጭ አዲስ አበባ ላይ ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮ-አሜሪካዊያን ሃኪሞች ቡድን አስታውቋል፡፡

የቡድኑ መሪዎች በሰጡት መግለጫ የሚገነባው ሆስፒታል ውጥን የኢትዮጵያንና የአካባቢዋን፣ አልፎም የመላ አፍሪካን የጤና አገልግሎት ደረጃ ትርጉም ባለው መልኩ የሚቀይር ማዕከል ማቋቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የላቀ ሙያና አገልግሎት ማዕከልም እንደሚመሠረት አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡