ሃምሣ ሺህ የሚሆኑ ሰዎችን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማስገባት የሚያስችል የዲቪ (Diversity Visa) ዕጣ መርሃ ግብር በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ለ2017 ዓ.ም መዘጋጀቱን አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ገለፀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
እነዚህ የዳይቨርሲቲ ቪዛዎች ግን በዓለም ሁሉ ላሉ በዕድሉ ለመጠቀም ለሚፈልጉ አገሮች መሆኑን የኤምባሲው ምክትል ቆንሲል ጃሽዋ ማርክስ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል።
ከአጠቃላዩ የቪዛ ብዛት እያንዳንዱ አገር ሊያገኝ የሚችለው እስከ ሰባት ከመቶ መሆኑንና ይህም ማለት ኢትዮጵያዊያን ሰባት ከመቶውን ድርሻ በሙሉ ያገኛሉ ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል።
ባለፉት አሥራ ሁለት ዓመታት 36 ሺህ 797 ኢትዮጵያዊያን በዚህ መርሃ ግብር አማካይነት ወደ አሜሪካ ማግባታቸው ታውቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5