የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች በባህዳር ቤተክርስቲያን ደጅ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ በለው ጃፎ ወረዳ የተፈናቀሉና በባሕርዳር ከተማ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሚገኙ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ በለው ጃፎይ ወረዳ በግጭት ምክኒያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ 527 አባወራዎች ባሕርዳር ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በልመና ላይ እንደሚገኙ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

በእርሻ፣ በከብት ማርባት እና በንግድ ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ ቁጥራቸው የበዛ ወጣቶች፣እናቶችና ሕፃናት ጭምር በቤተስርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት እንዲያቋቁማቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው አለማግኘታቸውን በመግለፅ አማረዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች በባህዳር ቤተክርስቲያን ደጅ