Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የሦስት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን፣ ዛሬ ማክሰኞ፣ ኅዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ በአማራ ክልል በግጭት፣ በትግራይ ደግሞ በቅድመ ሁኔታዎች ምክንያት ሥራውን ማስቀጠል እንዳልቻለ አስታውቋል።
ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፣ በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ መጠናቀቁን እና የኦሮሚያ ክልል በሦስት ሳምንታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡
የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ ሊጠናቀቅ የሚጠናቀቀው በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ሲኾን፣ የኮሚሽኑን ቆይታ የማራዘም ጉዳይ የምክር ቤቱ ውሳኔ መኾኑን ፕሮፌሰር መሥፍን ጥያቄውን ላነሱት የፓርላማ አባላት በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል።
ከምክር ቤቱ ለተነሱላቸው ጥያቄዎችም የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡