ለሰላማዊ ሰልፍ ሲዘጋጁ ታፈሰዉ የታሰሩት የረሃብ አድማ ጀመሩ
Your browser doesn’t support HTML5
ቅዳሜ ህዳር ሃያ ሰባት ጀምሮ በአዲስ አበባ ፓሊስ ታስረዉ የሚገኙ ሃምሳ ሁለት የዘጠኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር አመራርና አባላት ሕጋዊ መብቶቻችን የጠበቁ በማለት የረሃፍ አድማ ጀምረዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ ዮናታን ተሰፋዬ ለቪኦኤ እንደገለጹት ታሳሪዎቹ በሕግ ጠበቃ የመወከል፣ በዘመድ የመጠየቅ መብታቸዉ መጣሱን በመቃወም የረሃብ አድማ ጀምረዋል። ከሰማያዊ ፓርቲ መሪ አቶ ይልቃል ጌትነት በተጨማሪ አንዳንዶቹም በጨለማና እጅግ ቀዝቃዛ ክፍል ዉስጥ የታሰሩ ሰለሆነ ሕጋዊ መብታችን ይከበርልን ማለታቸዉን ተናግረዋል። ከሰማኒያ አራት የማያንሱ የፓርቲዎቹ አባላት በአዲስ አበባ የተለዩ ፓሊስ ጣቢያዎች ታስረዉ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ዮናታን ቀደም ብለዉ የታሰሩት የእስረኛ መብታቸዉ የተከበረ መሆኑን አስምረዉበታል።