በኢትዮጵያ 1652 ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ  መገኘቱና  የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል

Ministry of Health Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ለ 22 ሺህ 252 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተካሂዶ 1652 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ተገልጿል
በተያያዘም በዚሁ የሃያ አራት ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከኮቪድ አስራ ዘጠኝ በተያያዘ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቋል፥ 11 በአዲስ አበባ በአስከሬን ምርመራ ሲገኙ ስድስቱ በአዲስ አበባ የህክምና ተቁዋም መሆኑን ለመረዳት ተችሏል
የጤና ሚኒስቴር በሰጠው ዕለታዊ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ይዞታ መረጃ ዛሬ ከተገኙት ውስጥ 977 ሰዎች የተገኙት አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን 202 ደግሞ በኦሮምያ ክልል መሆኑ ታውቋል፥ በትግራይ ክልል 196 በአማራ ክልል ደግሞ ዘጠና ሰዎች ተመዝግበዋል
በሲዳማ ክልል 75 ፥ በደቡብ ህዝቦች ክልል ደግሞ 48 ሰዎች ተገኝተዋል፥ 19 በድሬደዋ፥ 13 በአፋር 13 በጋምቤላ፥ 10 ሰዎች በሶማሌ፥ 6 ሰዎች በሃረሪ እንዲሁም 3 ሰዎች ቤንሻጉል ጉምዝ ክልል መገኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ዘርዝሯል