የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዛሬ ውሎና ክስ ያልተነሳላቸው የዞን ዘጠኝ አምደኞች ጉዳይ

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

Your browser doesn’t support HTML5

የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሎና ክስ ያልተነሳላቸው የዞን ዘጠኝ አምደኞች ጉዳይ

የፌድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት ክስ ባልተነሳላቸው የዞን ዘጠኝ አምደኞች ጉዳይ ዛሬ ብይን ይሰጣል፤ ተብሎ ቢጠበቅም ለሌላ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሾች የተለያዩ አቤቱታዎችን ለችሎቱ አቅርበዋል።

በሌላ ዜና በዚሁ ችሎት ብይን ከእስር እንዲፈቱ ባለፈው ሳምንት ትዕዛዝ የተሰጠላቸው የቀድሞው የአንድነት የአመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌው እና ሰባተኛው ተከሳሽ አቶ አብረሃም ሰለሞን እስከ ዛሬም ከእስር አልተፈቱም።

የፍርድ ቤቱ ብይን በአቃቤ ሕግ የይግባኝ አቤቱታ መታገዱ ነው፤ የተነገረው። በጉዳዩ ላይ የሕግ አስተያየት ባለ ሞያዎች ግን እግዱ የሕግ መሠረት የለውም ይላሉ።