የግንቦት ሠባት ተጠርጣሪዎች የችሎት ውሎ

በግንቦት ሠባት ድርጅት ውስጥ በማንኛወም ሁኔታ ተሣትፋችኋል ተብለው የሽብር ክሥ የተመሠረተባቸውን ዘጠኝ ሰዎች ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ለሌላ አንድ ወር ቀጠረ፡፡

በእነ ትንሣዔ በርሶ መዝገብ የተከሰሱ ዘጠኝ ሰዎች ጉዳይ ለበርካታ ጊዜያት በቀጠሮ ሲተላለፍ የቆየና ዛሬ ብይን ይሰጣል፣ ተብሎ ሲጠበቅ እንደነበር ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የፍርድ ቤት ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡

ዳኞች ባለመሟላታቸው ብይኑ አልተዘጋጀም በሚል ፍርድ ቤቱ ለፊታችን ታኅሣስ ስድስት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ከተከሣሾቹ አራቱ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ፍሬው ተክሌ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬና ቴዎድሮስ አስፋው በጠበቃ ስላልተወከሉ በቀጠሮ መራዘም ላይ ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ፍሬው ተክሌ በሚባለው ተከሣሽ በፅሁፍ ሊያቀርብ የነበረውን አቤቱታ ማረሚያ ቤቱ ከልክሎኛል ሲል አመልክቷል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የግንቦት ሠባት ተጠርጣሪዎች የችሎት ውሎ