በ“ብሔር ብሔረሰቦች ቀን” መከበር ምሁራን የሕገ መንግሥቱን ሚና ይጠይቃሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በ“ብሔር ብሔረሰቦች ቀን” መከበር ምሁራን የሕገ መንግሥቱን ሚና ይጠይቃሉ

አኹን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ሕገ መንግሥት የጸደቀበት ኅዳር 29 ቀን፣ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን እየተባለ በየዓመቱ የሚዘከር ሲኾን፣ ዘንድሮም ለ18ኛ ጊዜ፣ ነገ ቅዳሜ፣ በጅግጅጋ ከተማ እንደሚከበር ተገልጿል።

የዕለቱ መከበር፣ ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎላ ነው፤ የሚባለውን ያህል፣ ማንነት ተኮር እንደኾነ የሚገለጸው ሕገ መንግሥት፣ አኹን በኢትዮጵያ ለሚታየው መገፋፋት እና የግጭት መበራከት አንዱ ምክንያት እንደኾነ በመጥቀስ፣ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፤ የሚሉም አሉ።

ተቺዎቹ፣ የሕገ መንግሥቱን መሻሻል እንደ ማዕዘናዊ መፍትሔ ሲያቀርቡ፤ ሕገ መንግሥቱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን አረጋግጧል፤ ባዮቹ ደግሞ፣ መፍትሔው፥ እውነተኛ ፌዴራላዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትን መለማመድ ነው፤ ሲሉ ይሞግታሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።