ለውጭ ገበያ ላቀረቡት ቡና ክፍያ አለማግኘታቸውን ነጋዴዎች ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

ለውጭ ገበያ ላቀረቡት ቡና ክፍያ አለማግኘታቸውን ነጋዴዎች ገለጹ

“ቨርቲካል” በተሰኘ የገበያ ሰንሰለት የቡና ምርታቸውን ለውጭ ግብይት ማቅረባቸውን የገለጹ አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ክፍያ ስላልተፈፀመላቸው ከገበያ እየወጡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ እና ነጋዴዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ ሻፊ ዑመር ደግሞ፣ የቡና ግብይት ሥርዓቱን በሚያዛቡት ላይ ባለሥልጣኑ ርምጃ መውሰዱን አስታውቀዋል፡፡

ባለሥልጣኑ፣ በዘንድሮ 2016 ዓ.ም. 1ነጥብ7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ቡናን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ማቀዱን ምክትል ኃላፊው ጠቁመው፣ እስከ አሁን ከቀረበው ቡና ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።