የኢትዮጵያ መሪዎች ካስትሮን “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ” አሏቸው

  • እስክንድር ፍሬው

የዚያድ ባሬ ጦር ኢትዮጵያን በምሥራቅና በደቡብ ወርሮ የነበረባቸው አካባቢዎች

“በአስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ” ሲሉ ፊደል ካስትሮን የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኩባው መሪ በኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል፡፡

ኩባን ለግማሽ ምዕት ዓመት በመሩት ፊደል ካስትሮ ኅልፈት ማዘናቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ውለታቸውን አስታውሰው በተለይም በሶማሊያው ዚያድ ባሬ ወረራ ወቅት ስላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ ታላቅ ወዳጅና መሪ ነበሩ፤ ውለታቸውም ከትውልድ ትውልድ ሲታወስ ይኖራል” ብለዋል፡፡

ፊደል ካስትሮ

በኢትዮጵያና በኩባ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትም “በደም የጠበቀ” ብለዋታል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመም ተመሣሣይ የኀዘን መግለጫ አስተላልፈዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መሪዎች ካስትሮን “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ” አሏቸው