አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ለብዙዎች እስር ሲሆን ከታሳሪዎቹም ጋዜጠኞች እና ጦማርያን ይገኙበታል

የኢትዮጵያው አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ተጀምሮ በተለይም በሰሜኑ የአማራው ክልል ከነበረው ሕዝባዊ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ለብዙ ሺሕ ሰዎች ወህኒ መውረድ ምክንያት ሆኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል ጋዜጠኞችና ጦማርያን ይገኙባቸዋል።

የኢትዮጵያው አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ባለፈው ዓመት በኦሮሚያ ክልል ተጀምሮ በተለይም በሰሜኑ የአማራው ክልል ከነበረው ሕዝባዊ አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ለብዙ ሺሕ ሰዎች ወህኒ መውረድ ምክንያት ሆኗል። ከታሳሪዎቹ መካከል ጋዜጠኞችና ጦማርያን ይገኙባቸዋል።

ማርቲ ቫንዳር ወልፍ ከዛሬው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ቀደም ብላ፣ ከሦስቱ የኢትዮጵያ ብሎገሮች ጋር ያደረገችውን ውይይት፣ ለቪኦኤ ልካለች፡፡

በዘገባውም የዩኒቨርሲቲ መምህርና ሃያሲ ሥዩም ተሾመ፣ ለጀርመኑ ራድዮ ጣቢያ ዶቼ ቬሌ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ የመንግሥቱን እንከን በመናገራቸው፣ በጥቅምት ወር ለሁለት ወራት እስር ቤት ቆይተዋል።

ከተፈቱ በኋላም፣ በሳምንት በተደጋጋሚ ጊዜያት በተለያዩ የፖለቲካ ዓምዶችና ማኅበራዊ ድረ ገፆች ላይ ፁሑፎችን አውጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ለብዙዎች እስር ሲሆን ከታሳሪዎቹም ጋዜጠኞች እና ጦማርያን ይገኙበታል