የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እየላከ ነው

  • እስክንድር ፍሬው

የምግብ አቅርቦትና መድኃኒት የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች መቀሌ አዲግራት እና ሽሬ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለ ውጊያ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንቅፋት ሆኗል በሚል የሚሰጡ አስተያየቶችንም ሐሰት በማለት አጣጥሏል።

በሽሽት ላይ ከሚገኙ የሚሊሻ አባላት ጋር አልፎ አልፎ የሚደረግ የተኩስ ልውውጥና ወንጀለኞችን ለመያዝ የሚደረግ ጥረት እንደ ውጊያ አይቆጠርም ነው ይላል መግለጫው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እየላከ ነው