የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ለዓመታት ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ምሽግ ውስጥ በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀምጠው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለፁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያና በኤርትራ ምስራቃዊ አዋሳኝ የደባይ ሲማ ቡሬና በሰሜን የሰረሃ ዛላአንበሳ ኬላዎች በሁለቱ ሀገር መሪዎች ዛሬ በይፋ ተከፍተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወቂ ዛሬ ሁለቱን መተላለፊያዎች በይፋ ከከፈቱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መግለጫ ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግለጫ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እጅግ በጣም ደስ የሚል ጊዜ እንደነበራቸው ተናግረዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5