ኢትዮጵያዊው ከሃያ ዓመታት በኋላ የኤርትራዊያኑን ቤት አስረከቡ

ኤርትራዊያኑ በኢትዮጵያ

ኤርትራዊያኑ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተከሰተው ጦርነት ፖለቲካዊ ቀውስን ያስከተለ ማኅበራዊ ጠባሳ የፈጠረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በዘር በኃይማኖት አንድ የነበረ ህዝብ በማይታይ አጥር ተከልሎ በናፍቆት ሰቀቀን ሁለት አሥርት ዓመታትን ተሸግሯል፡፡

በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዳግም ሲታደስ ከብዙሃኑ ፊት ላይ የሚወርደው እምባ፣ የሚሰማው ሲቃ ከቃላት በላይ የሚናገረው ቁም ነገር ነበር፡፡

አቶ ደመቀ በለው የተባሉ በደቡብ ወሎ ዞን የኮምቦልቻ ከተማ ኗሪ ሰሞኑን ታሪካዊ ሥራ ከውነዋል፤ ለ20 ዓመታት ተከራይተውበት የነበረውን የኤርትራዊያን መኖሪያ ቤት ጠብቀው ለህጋዊ ባለንብረቱ በማስረከብ፡፡ ዳግም የኅዝቦች ግንኙነት በፍቅር ታድሷል፡፡ በታማኝነት ተሟሽቷል፡፡

በርክክቡ ላይ የመንግሥት አካላት፣ የአካባቢው ኗሪዎችና የቅርብ ቤተሰቦች ታድመው ነበር፡፡

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያዊው ከሃያ ዓመታት በኋላ የኤርትራዊያኑን ቤት አስረከቡ