የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ሰማኒያ ዓለምቀፍ በረራዎችን አቋረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገዱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ወደ 80 ዓለምቀፍ በረራዎቹን ማቋረጡን ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

በዓለምቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የካርጎ /የዕቃ ማመላለሻ/ በረራዎች እንደቀጠሉ ጠቁሞ፣ ዕርምጃው የተወሰደው የኮሮናቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መሆኑንም አስታውቋል።

የሀገር ውስጥ በረራ ተጓዦች ቁጥር በ50 በመቶ መቀነሱን፣ ወደ ሁሉም የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹ የሚሰጠውን አገልግሎት አለማቋረጡን ጭምሮ ገልጿል።