ሙሳፋኪ ማሃማት የጠ/ር ዐብይን ሽልማት አደነቁ

  • እስክንድር ፍሬው
Moussa Faki And PM Abiy Ahmed

Moussa Faki And PM Abiy Ahmed

"የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ያሸነፉት የኖቤል ሽልማት አፍሪካውያን ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ማምጣት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ነው" ሲሉ ሙሳፋኪ ማሃማት ተናገሩ።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ ማሃማት ይህን የተናገሩት በኖቤል ሽልማቱ የተሰማውን ደስታ ለመግለፅ የሰላም ሚኒስቴር ባዘጋጀው ሥነ- ስርዓት ላይ ነው።

በተለይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን አስተዋፆዖ ያደረጉትን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ያመሰገኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በበኩላቸው ፕሬዚዳንቱ በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ የሚሄዱበት ቀን እንዲመጣ ፀልዩ ሲሉ ለኢትዮጵያውያን መልዕክት አስተላለፈዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሙሳፋኪ ማሃማት የጠ/ር ዐብይን ሽልማት አደነቁ