አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ቁጥራቸው እንኳን በውል የማይታወቅ የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን አምኖ ሁሉንም እንዲፈቱ ማድረግ ካልተቻለ የተባለውን ሀገራዊ መግባባት ፈጽሞ እንደማያመጣ ዴሞክራሲንም እንደማያሰፋ ተናግረዋል።
ገዢው የኢትዮጵያ ፓርቲ ኢሕአዴግ ለ18 ቀናት ካደረገው ግምገማና ግምገማውን ተከትሎ በጹሑፍ ካወጣው መግለጫ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ የአራቱ ፓርቲ አመራሮች በጋራ የሰጡት መግለጫ በድምፅ ከመሰማቱ በፊት በማኅበራዊና በዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛ ለሰዓት ሲሰራጭ የቆየው ዜና የተምታታና የተዛባ ትርጓሜን ሲሰጥ ቆይቷል።
ይህም መንግሥት “ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ ማዕከላዊም ይዘጋል” የሚል አንደምታ ያለው ዜና ሲሆን ይህን ተከትሎ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ሳይቀሩ መንግስት የወሰደው እርምጃ ጥሩ ነው የሚል ይዘት መግለጫን አውጥተዋል።
ቆየት ብሎ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እንዲህ ያለ ይዘት እንደሌለው ንግግሩም “በፍርድ ቤት የተፈረደባቸው ወይ ደግሞ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው እና ጉዳያቸው እየተጣራ የሚገኙ የፖለቲካ አመራሮችም ሆነ ግለሰቦች በሰሩት ጥፋት መሰረት ይሄ እየተካሄደ እንዳለ የሚታወቅ ነው ነገር ግን የተሻለ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር እንደዚሁም የዴሞክራሲ ምሕዳራችንን የበለጠ እናሰፋለን ብለን ባልነው መሰረት አንዳንዶቹ ክሳቸውም ተቋርጦ እንደዚሁም ደግሞ የምሕረት ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ምሕረት ተደርጎላቸው ሕጉና ሕገ መንግሥቱ እና የሕግ አሰራር ሥርዓታችን በሚፈቅደው መሰረት ተጣርቶ የሚወሰዱ እርምጃዎች ይኖራሉ የሚል እምነት አለን ስለዚህ ይሄ የሕግ የበላይነት በማይጥስበት ሁኔታና ሕግና ሥርዓቱን ተከትሎም ቢሆን ነገር ግን የዴሞክራሲ ምሕዳራችንን የፖለቲካ ምሕዳራችንን ለማስፋት እንደዚሁም ደግሞ የሚፈጠረው መንፈስ መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ ሥርዓታችንን ሊያጎለብት በሚችልበት ደረጃ የሚስተናገድ ነው የሚሆነው”የሚል ነው።
የአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት አዘጋጅ ፀዳለ ለማና የቀድሞ አዲስ ነገር ጋዜጠ አዘጋጅ መስፍን ነጋሽን በዚህ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።
Your browser doesn’t support HTML5